Name of missing person (በውጭ ሃገር የጠፋብዎን ሰው ስም): Meseret Tadele Diribsa Last known location (ከመጨረሻ የነበሩበት ቦታ): Riyadh, Saudi Arabia Contact name (of family doing the search) (የተጠሪ ሰው ስም): Teshome Tadele Diribsa Email to be contacted at and/or (ሊገኙ የሚችሉበት አድራሻ ወይም ኢ - ሜል): Email: ITETETESHE@GMAIL.COM Web: www.facebook.com/teshome.tadele Tel: +251912154920 Additional detail (ተጨማሪ መረጃ): ይህቺ የምትመለከቷት ወጣት እህቴ ነች፡፡ መሰረት ታደለ ትባላለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ ጊንጪ የምትባል ከተማ ውስጥ ነው ተወልዳ ያደገችው ፡፡ በ 1998 አካባቢ ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ ተነሳች፡፡ መጀመሪያ ጅቡቲ በመሄድ የተወሰነ ጊዜ እዛ ከቆየች በኋላ በባህር ላይ ተጉዛ ሳውዲ አረቢያ፣ ሪያድ ከተማ በመግባት ከ1998 እስከ ግንቦት 2003 ዓ.ም ድረስ ስትሰራ የቆየች ቢሆንም ከ ግንቦት 2003 ዓ.ም ጀምሮ እህቴ በህይወት ትኑር፣ አትኑር ምንም ማወቅ አልቻልኩም ፡፡ በተለይ እናታችን በዚህች እህታችን መጥፋት ምክኒያት በጣም የተጎዳችብን ስለሆን ይህ ጉዳይ ይመለከታቸዋል የተባሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመንግስት መ/ቤቶች ፣ ቀይ መስቀል እና በሌሎች መ/ቤቶች በኩል እንዲያፈላልጉልኝ ጥረት ባደርግም ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም ፡፡ ልትጠፋብን አካባቢም በጣም መታመሟን እና ሪያድ ያለው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ውስጥ የአምባሳደሩ ሠራተኛ ሆና ተቀጥራ መስራት እንደጀመረች እህቴ በስልክ ደውላ ነግራኛለች፡፡ ፀሐይ ለምትባል ጓደኛዋ ደውዬላት በዚህ ህመሟ ምክንያት አል ኢማን ሆስፒታል/ “Al Iman Public Hospital” የሚባል ቦታ እንዳደረሷት እና ጓደኛዋ የመኖሪያ ፍቃድ ስለሌላት የእህቴን ጉዳይ መከታተል እንደማትችል ከነገረችኝ በኋላ እህቴን በራሷ ስልክም ሆነ በጓደኛዋ ስልክ ላገኛት አልቻልኩም፡፡ ይህንና ሌሎች መረጃዎች ይዤ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የኢትዮጵያ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ጽ/ቤት በኩል እህቴን እንዲያፈላልጉልኝ ለአራት ዓመታት በተደጋጋሚ በመመላለስ ባመለክትም እስከ አሁን መፍትሔ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ስለዚህ እህቴን በማፈላለግ ሂደት ሁላችሁም እንድትተባበሩኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ |
0 Comments
Leave a Reply. |
List of missing migrants in Libya, Yemen, Lebanon, Sudan, South Africa and GCC countries.Please alert us if someone is found or has been evacuated at info@adega911.com Filter by tag
All
Archives |